Collection: የእጅ ጽሑፍ መልመጃ መጻፍት

የእጅ ጽሑፍ መልመጃ መጻፍ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይገኙበታል፡

- ተማሪዎች እንግሊዘኛ የሚጽፉ ከሆነ በቀጥታ መጻፍ መጀመር ይችላሉ እጅን በሚገባ በማፍታታት የእጅ ጽሑፍ በጥራት ያለማምዳል፣

- እንግሊዘኛ ቋንቋ ማንበብ የሚችሉ ሆኖም አማርኛ እየተናገሩ መጻፍ ለተቸገሩ ሁሉ የዚህን መጽሐፍ ፊደላት በማገናዘብ ካለአስተማሪ በራሳቸው የፈለጉትን ሀሳብ መጻፍ ይችላሉ፣ እንዲሁም በእንግሊዝኛ የተተረጎመ ስለሆነ ተማሪዎች ምን እንደሚጽፉ እንግሊዘኛውን በማንበብ ስለ ሀገራቸው ሀብት እግረ-መንገዱን ይረዱበታል፣

- በአስተማሪ ወይም በቤተሰብ አባል ለልጆች የእጅ ጽሑፍ ልምምድ የቤት ሥራ ገፅ ብዛት ማስረከቢያ ፎርም አካትቷል፣

- በማንኛውም ቦታ ካለመማሪያ ክፍልና ጥቁር ሰሌዳ ማንበብና መጻፍ ያስችላል፣

- ከታሪኩ ጠቃሚነት እና ተከታታይነት አኳያ ብዙ በመጻፍ በደንብ የእጅ ጹሑፍ ልምምድ እንዲያገኙ ያስችላል፣

- በተጨማሪም ሀገርን በሚጠቅም ከፍተኛ መጠን ያለውን የውኃ ሀብታችንን ለማስተዳድር የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ሂደቶችን በማስረዳት፤ ብሎም የጣና ሀይቅንና የዝናብ ውኃ ሀብት ትስሥርን እግረ-መንገዱን በቀጣይነት በማብሰር እስከ ትግበራ ድረስ ይዘልቃል።